አሽከርካሪ / Driver

GlobeDock PLC · 2 days ago
Location
Addis Ababa HQ
Department
Operations
Employment Type
Full-Time

የሥራው ዋና ዓላማ

የድርጅቱን የዕለት ተዕለት የውጭ ጉዳዮች (የመንግሥትና የባንክ ሂሳብ ሥራዎች፣ የሰነድ ዝውውር) በግንባር ቀደምትነት ማከናወን እና ከተመደበው ተሽከርካሪ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የትራንስፖርት አገልግሎቶች በጥንቃቄና በታማኝነት መስጠት።


ዋና ዋና ኃላፊነቶች


የማሽከርከር እና የተሽከርካሪ እንክብካቤ: (Driving)


* የድርጅቱን ሰራተኞች እና እንግዶች በተመደበው መርሃ ግብር መሠረት በጥንቃቄ ማጓጓዝ።

* የተሽከርካሪውን የዘወትር የቴክኒክ አቋም፣ ንጽህና፣ የቦሎ እና የኢንሹራንስ እድሳት መከታተል።

* የነዳጅ አጠቃቀምን እና የጉዞ መዝገብን (Logbook) በአግባቡ መያዝ።


የጉዳይ ማስፈጸም ሥራዎች (Liaison):


* የድርጅቱን ደብዳቤዎች፣ ውሎች፣ ደረሰኞች እና ሰነዶች ለደንበኞች፣ ለጋራ አጋሮች እና ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥንቃቄ ማድረስና መከታተል።

* የባንክ ገቢ/ወጪ፣ የቼክ ልውውጥ እና የውሃ/መብራት/ቴሌ ክፍያዎችን ማከናወን።

* ከክፍለ ከተማ፣ ታክስ/ገቢዎች እና ሌሎች መሥሪያ ቤቶች ጋር ያሉ መደበኛ የቢሮ ጉዳዮችን መከታተል እና ማስፈጸም።



የሥራው መስፈርቶች

* ትምህርት፡ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ።

* መንጃ ፈቃድ፡ ሕጋዊና የታደሰ 3ኛ ደረጃ፣ ሕዝብ 1 ወይም ደረቅ ጭነት 1 የመንጃ ፈቃድ ያለው።

* የሥራ ልምድ፡ በሹፌርነት እና በጉዳይ አስፈጻሚነት በትንሹ 1 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው/ላት።



ችሎታና ስነ-ምግባር፡

* ለአሠራር ግልጽ የሆኑ የአዲስ አበባ መንገዶችን፣ የመንግሥት ቢሮዎችን እና የባንክ አሠራሮችን በደንብ የሚያውቅ።

* ከፍተኛ ታማኝነት፣ ሰዓት አክባሪነት እና ግልጽ የኮሙኒኬሽን ችሎታ ያለው።